የጤና ሚኒስቴር የህብረተስብ ጤና አደጋዎችና በሽታዎች አስቀድሞ መከላከልና መቆጣጠር ላይ ከአሜሪካ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር (CDC) ጋር የትብብር ስራውን አጠናክሮ መቀጠል በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ዉይይት አድርገዋል

  • Time to read less than 1 minute
CDC

በውይይቱ ወቅት፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ከCDC ጋር ለረጅም ጊዜ የተገነባው ትብብር በጤና ስርአት ማጠናከር፣ በኤች አይ ቪ ኤድስና በወባ ፕሮግራሞች እንዲሁም በላብራቶሪ አቅም ግንባታ ዘርፍ ያስመዘገበውን ግልጽ ውጤት በማስታወስ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።


በቀጣይም ይህ ትብብር በተለይ በድንገተኛ አደጋዎች ዝግጁነት እና ምላሽ አሰጣጥ ስርዓትን ማጠናከር እንዲሁም በክትባት አገልግሎት እና በመረጃ ስርዓት ማዘመን ዘርፎች ላይ በይበልጥ እንዲጠናከር ጠይቀዋል። 


የግሎባል ሄልዝ ሴንተር ሪጂናል ዳይሬክተር ማርታ አከርስ በበኩላቸው የአሜሪካ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር (CDC) የኢትዮጵያ የጤና ስርአትን ለማጠናከር መስራቱን እንደሚቀጥል በመግለፅ፣ የጤና ሚኒስትር የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በተለይ በበለጠ ቅርበት አብረው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።


ወይይቱ በቀጣይም ይህ ትብብር በተለይ በድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና ምላሽ፣ በክትባት አገልግሎት እና በመረጃ ስርዓት ማዘመን ዘርፎች ላይ ይበልጥ እንዲጠናከር ከስምምነት በመድረስ ተጠናቋል።