ለመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያዎች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

ራዕይ

ጤናማ ፣ አምራችና የበለፀገ ማህበረሰብን መፍጠር

ተልዕኮ


ጠንካራ የመድሃኒት ቤት አገልግሎትን ማቋቋም ፣ የፀረ ተሕዋስያን መድሃኒት መቋቋምን (AMR) መከላከል እና መቆጣጠር፣ የሀብት ብክነትን የሚቀንስና በአገሪቱ ውስጥ ደህንነቱና ጥራቱ የተጠበቀ ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው የህክምና ግብዓቶች አቅርቦትን የሚያረጋግጥ ጠንካራ የአቅርቦት ሰንሰለትና የጤና አገልግሎት ቴክኖሎጂ አስተዳደር ስርዓትን ማቋቋም፣ መደገፍና ማስተዳደር።

ዓላማ

በዘመናዊና የተረጋገጡ የአሠራር ዘዴዎች እና ስርዓቶች በመደገፍ በጤና ተቋማት ውስጥ ውጤታማ የመድኃኒት ቤት አገልግሎትን እውን ማድረግ

ዘመናዊ የአስተዳደር ሥርዓትን ተጠቅሞ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ሂደት ከግዥ ዕቅድ እስከ አፈፃፀም ድረስ በማመቻቸት የጤና ተቋማት ትክክለኛና ጥራት ያላቸውን የመድኃኒት ምርቶች እንዲኖራቸው ማድረግ

የማህበረሰቡን ፍላጎት መሠረት ያደረገና ብክነትን እና የተበላሹ ሂደቶችን የሚከላከል የፋርማሲ አገልግሎት መፍጠር፤ ግልፅነትን እና ተጠያቂነትን በሚያበረታታ መልኩ አጠቃላይ የመድኃኒት አገልግሎትን ማቋቋም 


ወጪ ቆጣቢ፣ የጥራት ስታንዳርዶችን የሚያሟሉ፣ የጤና አገልግሎት አቅራቢዎችና ማህበረሰቡ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት የማያደርሱ የሕክምና መሣሪያዎችን ለማቅረብ ውጤታማ የጤና አገልግሎት ቴክኖሎጂ አስተዳደርን ማቋቋም። ይህም የሚሳካው የጤና አገልግሎት ቴክኖሎጂ ፍላጎቶችን በመገምገም፣ በጤና ተቋማት ደረጃ የህክምና መሳሪያዎች ተገቢ አያያዝ እንዳላችው በማራጋገጥና ጥራት ያለውን የጤና አገልግሎት በመደገፍ ነው።


የመድኃኒት እና የሕክምና መሣሪያዎች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሚናዎች


የመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያዎች ዘርፍ ፖሊሲን ፣ ስትራቴጂን ፣ ፍኖተ ካርታውን ፣ መመሪያዎችን ፣ ፕሮቶኮሎችን እና መደበኛ የአሰራር ሂደቶችን የተሳካ ትግበራ መመስረትና መቆጣጠር

የመድኃኒት ፖሊሲን፣ የመደበኛ ሕክምና መመሪያን፣ የብሔራዊ አስፈላጊ ሕክምናን እና የሕክምና ዕቅድ ዝርዝርን አፈፃፀም መመስረት፣ በየጊዜው ማደስ እና መቆጣጠር

የፋርማሲ አገልግሎት እንቅስቃሴዎችን (ኦዲት የሚደረግ የመድኃኒት ግብይት እና አገልግሎቶችን ፣ ክሊኒካዊ የፋርማሲ አገልግሎቶችን ፣ሞዴል የማህበረሰብ ፋርማሲን ፣ የመድኃኒት መረጃ አገልግሎትን ፣ ስቴራይል የሆኑና ያልሆኑ የመድሃኒት ማዋሃድ አገልግሎቶችን) መምራት ፣ መደገፍ ፣ ማስተባበር እና መከታተል።

ምክንያታዊ የሆነ የመድሃኒት አጠቃቀምን ማበረታትና የፀረ -ተህዋሲያን መድሃኒት መቋቋምን መከላከልና እንዳይስፋፋ መስራት

የክልል ጤና ቢሮዎችንና የጤና ተቋማትን ዓመታዊ የQUANTIFICATION EXERCISES እንዲያካሂዱ መደገፍ

በጤና ተቋማት ውስጥ አስፈላጊ መድሃኒቶች ፣ አቅርቦቶች እና ሬጀንቶች መኖራቸውን ማረጋገጥ

የአገር ውስጥ የመድኃኒት እና የሕክምና መሣሪያ ማምረቻዎችን ማበረታት

በመድኃኒት ፣ በሕክምና መሣሪያ እንዲሁም በባህላዊ መድኃኒቶች ላይ የመንግስትን የግል አጋርነትን ማጠንከር።

ከክልል ጤና ቢሮዎችና ከጤና ተቋማት የመጡ ባለሙያዎችን በፋርማሲ አገልግሎት ፣ በባህላዊ መድኃኒት ፣ በአቅርቦት ሰንሰለት እና በሕክምና መሣሪያ አያያዝ ላይ የአቅም ግንባታ ማቅረብ።

የመድኃኒት እና የህክምና መሳሪያዎችን ተደራሽነት እና ጥራት ለማሻሻል ፣ እንዲሁም በአስቸኳይ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተባብሮ መስራት

ከዩኒቨርሲቲዎች እና ከአጋሮች ጋር በመተባበር በመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ፣ በፋርማሲ አገልግሎት ፣ በፀረ -ተሕዋስያን መድሃኒት መቋቋም ፣ በባህላዊ ህክምና ሙያ እና በሕክምና መሣሪያ አያያዝ ላይ የሚደረጉ ግምገማዎችን ማስተባበር።

በሁሉም ደረጃዎች ሙሉ የመረጃ ታይነትን ለማረጋገጥ የመድኃኒት እና የህክምና መሣሪያ አስተዳደር የኢንፎርሚውሽን ስርዓቶችን ማጠናከር

የሕክምና መሳሪያዎችን ዕቅድ ፣ የፍላጎት ግምገማ ፣ በጀት ምደባ ፣ ግዥ ፣ ስርጭት ፣ አወቃቀር፣ አጠቃቀም ፣ ጥገና ፣ እና አወጋገድ መከታተል

የሕክምና መሣሪያዎች የልህቀት ማዕከል ፣ የመነሻ ዕድገት መድረክና የማሻሻያ ማዕከላት መቋቋምን ማመቻቸት

የባህላዊ እና ዘመናዊ ሕክምና ውህደትን ማበረታት

የመድኃኒት እና የሕክምና መሣሪያን ፣ የፀረ ተሕዋስያን መድሃኒት መቋቋምን (AMR) እና ባህላዊ መድኃኒቶችን ብሔራዊ የምክክር መድረኮች መምራት/ማስተባበር

 

ዳይሬክቶሬት ተነሳሽነት

  • ኦዲት መደረግ የሚችል የመድኃኒት ግብይት እና አገልግሎቶች
  • የመድኃኒት እና ቴራፒ ኮሚቴ
  • ክሊኒካል ፋርማሲ አገልግሎቶች
  • የተዋሃዱ አገልግሎቶች
  • የረጅም ጊዜ ክትትል የፋርማሲ አገልግሎቶች
  • የመድኃኒት መረጃ አገልግሎቶች
  • ፀረ ተሕዋሳት ተቆጣጣሪ ፕሮግራም
  • የፀረ ተሕዋስያን መድሃኒት መቋቋምን መከላከልና መቆጣጠር
  • የጤና  አስተዳደር መረጃ ስርዓት (DAGU)
  • ብሔራዊ የመድኃኒት እና የሕክምና መሣሪያዎች ክትትል እና ግምገማ
  • የሕክምና መሣሪያዎች ስርጭት
  • የጤና አገልግሎት ቴክኖሎጂ ግምገማ (HTA)
  • የሕክምና መሣሪያዎች አስተዳደር የመረጃ ስርዓት
  • የተገላቢጦሽ ሎጂስቲክስ
  • የአደጋ ጊዜ አቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር
  • ባህላዊ ሕክምና