በ2030 እ.ኤ.አ. በሀገር አቀፍ ደረጃ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን ለማሳካት የሚያግዝ የቃል መግቢያ ሰነድ ይፋ ተደረገ
ይህ የቤተሰብ እቅድ 2030 የቃል መግቢያ ሰነድ አለም አቀፋዊ ሲሆን 69 ሀገራት የሚሳተፉበት ነው።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንደተናገሩት በ2030እ.ኤ.አ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎትን በሀገርአቀፍ ደረጃ ለማሳካት በምንገባው ቃል መሰረት የእናቶችና የህፃናትን ጤና ብሎም የአፍላ ወጣቶችንና የወጣቶችን ስነ-ተዋልዶ ጤና በማሻሻል የተሻለ ጤናማ ዜጋ በመፍጠሩ ረገድ መንግስት ሰፊ ስራ መስራት እንዳለበት ገልጸዋል:: የሁሉንም ተሳትፎ ባካተተ መልኩ የተዘጋጁት የጤናዉ ፖሊሲ ስትራቴጂዎችና የማስፈጸሚያ ሰነዶችን ወደ ተግባር የመለወጥ ስራ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚያሰፈልግና በገባነው ስምምነት መሠረት ያሉብንን ተደራራቢ ጫናዎችን በመቋቋም ብሎም በጋራ በጥምረት በመስራት ጤናማ ትውልድን ለመፍጠር እና ጤናማ ሀገርን ለመገንባት ይህ የቃል መግቢያ ሰነድ መዘጋጀቱንና ይፋ መደረጉን ተናግረዋል::