ሀገር አቀፍ የሐኪሞች ስፔሻሊቲ ስልጠና /ERMP/
ማስታወቂያ
የህክምና ዶክትሬት ዲግሪ ላላችሁና የስፔሻሊቲ ስልጠና መውሰድ ለምትፈልጉ በሙሉ፡-
የጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በ2015 የትምህርት ዘመን፤ በ22 የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች አመልካቾችን በብሄራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና መግቢያ ፈተና አወዳድሮ
ለማሰልጠን ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡ በመሆኑም ፍላጎት ባላችሁ የስፔሻሊቲ ትምህርት ዘርፍ ላይ በጤና ሚኒስቴር ድረ-ገፅ (www.moh.gov.et/ermp) መመዝገብና መወዳደር እንደምትችሉ አውቃችሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን የምዝገባ ጊዜውም ከጥቅምት 7-21 ቀን 2015ዓ.ም /October 17-31/2022/ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የፈተና ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን በተመለከተ ከላይ በተጠቀሰው ድረ-ገፅ ላይ ወደፊት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
ምዝገባውን ከመጀመራችሁ በፊት ዝርዝር መረጃዎችንና መመሪያዎችን እንድትመለከቱ እናሳስባለን፡፡
የጤና ሚኒስቴር እና የትምህርት ሚኒስቴር !!!