Articles

በ2030 እ.ኤ.አ. በሀገር አቀፍ ደረጃ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን ለማሳካት የሚያግዝ የቃል መግቢያ ሰነድ ይፋ ተደረገ 

family planning

ይህ የቤተሰብ እቅድ 2030 የቃል መግቢያ ሰነድ አለም አቀፋዊ ሲሆን 69 ሀገራት የሚሳተፉበት ነው። 


በመድረኩ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንደተናገሩት በ2030እ.ኤ.አ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎትን በሀገርአቀፍ ደረጃ ለማሳካት በምንገባው  ቃል መሰረት የእናቶችና የህፃናትን ጤና ብሎም የአፍላ ወጣቶችንና የወጣቶችን ስነ-ተዋልዶ ጤና  በማሻሻል የተሻለ ጤናማ ዜጋ በመፍጠሩ ረገድ መንግስት ሰፊ ስራ መስራት እንዳለበት ገልጸዋል:: የሁሉንም ተሳትፎ ባካተተ መልኩ የተዘጋጁት የጤናዉ ፖሊሲ ስትራቴጂዎችና  የማስፈጸሚያ ሰነዶችን ወደ ተግባር የመለወጥ ስራ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚያሰፈልግና  በገባነው ስምምነት መሠረት ያሉብንን ተደራራቢ ጫናዎችን በመቋቋም ብሎም በጋራ በጥምረት በመስራት ጤናማ ትውልድን ለመፍጠር እና ጤናማ ሀገርን ለመገንባት ይህ የቃል መግቢያ ሰነድ መዘጋጀቱንና ይፋ መደረጉን ተናግረዋል:: 

ጥራት ያለውን የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ ተጠየቀ

universal health coverage day

ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ቀን /INTERNATIONAL UNIVERSAL HEALTH COVERAGE COMMEMORATION DAY/ “የጤና ኢንቨስትመንት ለሁሉም" /INVEST IN HEALTH SYSTEMS FOR ALL/ በሚል መሪ ቃል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው፡፡ 


ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ቀን ሲከበር አጋር አካላት አጋርነታቸውን በመቀጠል በጦርነት የወደሙ ጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋምና ለአገልግሎት ብቁ ለማድረግ እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡

ከፍተኛ ውድመት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት ለማቋቋምና መልሶ ስራ ለማስጀመር እንዲቻል ከጤና ሚኒስቴር የቀረበ  ሁሉን-አቀፍ የድጋፍ ጥሪ!

Health Facility

አሸባሪው የጥፋት ቡድን ህወሓት በወረራ ይዟቸው በነበሩ አካባቢዎች ካደረሰው ሰብዓዊና ሞራላዊ ጥፋት በተጨማሪ  ህዝብ የሚገለገልባቸውን የጤና አገልግሎት ሰጪ ተቀቋማት፤ የህክምና ግብዓት ማከማቻ ተቋማትን እና ሌሎች ማህበራዊ ተቋማት አውድሟል፡፡ የህክምና መሳርያዎችን እና ሌሎች ግብዓቶችንም ጭኖ በመውሰዱ ዝርፍያ እና ጉዳት ፈጽሟል፡፡

 
በጤና ተቋማት ላይ የደረሰው ወድመት በተለይ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የመሰረታዊ እና ድንገተኛ ህክምና አግልግሎት አሰጣጥ በእጅጉ አስተጓጉሏል። እስካሁን በደረስንበት መረጃ ከ2700 በላይ የሚሆኑ የጤና ተቋማት አገልግሎት የማይሰጡ ሲሆን በአሁን ወቅት በመንግስት ተደራሽ ያልሆኑ አከባቢዎች ሲካተቱ ዉድመት የደረሰባቸዉ ቁጥር ከዚህ እንደሚያሻቅብ ይጠበቃል።