የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት
የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት (WCYAF) ከሌሎች ዳይሬክቶሬቶች ፣ ከፌዴራል ሆስፒታሎች፣ ከኤጀንሲዎች እንዲሁም ከክልልና ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ መዋቅሮች ጋር በቅርበት በመስራት አብዛኛዎቹን የሥርዓተ-ፆታ ፣ የሕፃናት ፣ የወጣቶችና የአካል ጉዳተኞች ሥራዎችን የማስተባበርና የመምራት ኃላፊነት አለበት። በዚህም የሴቶች፣ ወንዶች ፣ ወጣቶችና የአካል ጉዳተኞችን የጤና አገልግሎት እኩል ተጠቃሚነት ያረጋግጣል::
ዳይሬክቶሬቱ በሁሉንም የጤና ስርዓት ደረጃዎች ላይ ከ ሥርዓተ-ፆታ፣ ሕፃናት ፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ጋር የተዛመዱ ጉዳዮች ተገቢ ትኩረት መሰጠቱን ለማረጋገጥ ሁሉንም መዋቅሮቹን (4 የፌዴራል ሆስፒታሎች ፣ 7 ኤጀንሲዎች እንዲሁም 2 የከተማ አስተዳደር እና 10 የክልል ጤና ቢሮዎች ) ሲደግፍ ቆይቷል።