Articles

የአፍሪካን የክትባት እና የሕክምና ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያለመው ግዙፉ "ACHIEVE Africa" የተሰኘ ኢኒሼቲቭ ከ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን በይፋ ተመሠርቷል 

Dr Mekdes Daba

​በኢኒሼቲቩ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ በ2040 የክትባት ፍላጎትን 60 በመቶ በአህጉር ውስጥ ለማሟላት ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች መሆኑን የገለጹ ሲሆን መንግስት የመድኃኒት ግዥ ስርዓቱን በአገር ውስጥ ለሚመረቱ ምርቶች ቅድሚያ እንዲሰጥ በማሻሻሉ፣ በዘርፉ የአገር ውስጥ ፍላጎትን ሽፋን ከ8 በመቶ ወደ 42 በመቶ ማደጉን ጠቁመው በቀጣይ አምስት ዓመታት ወደ 60 በመቶ ለማሳደግ ታቅዶ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
\
​ኢትዮጵያን የፈጠራ ማዕከል (Innovation Hub) ለማድረግ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር መቅደስ የሀገሪቱ የክትባት የማምረት ጉዞ አሁን ላይ "ይሳካል ወይ?" የሚለው ጥያቄ ቀርቶ "እንዴት እና በምን ፍጥነት?" ወደሚለው ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩን አስታውሰዋል። 

ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ የጤና ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የጎንዮሸ ስብሰባ መካሄድ ጀምሯል

Dr Mekdes Daba

"የአፍሪካን የጤና ደህንነት እና የሉዓላዊነት አጀንዳ ማራመድ፡ ቁርጠኛ ፋይናንስ እና አመራርን በመጠቀም ዘላቂነትን ማረጋገጥ" በሚል መሪ ቃል የአፍሪካን የጤና ስርዓቶች በዘላቂ ፋይናንስ፣ ጠንካራ አመራር እና በራስ መተማመንን ለማረጋገጥ በተሻለ አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከር ላይ ያተኮረ የጎንዪሽ  ስብሰባ በአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል( Africa CDC) እየተካሄደ ይገኛል። 

በስብሰባው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌድሪ የጤና ሚኒስትር እና በአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል( Africa CDC) የቦርድ ም/ሰብሳቢ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ዝግጅቱን “የአመራር ቁርጠኝነት ማሳያ” ሲሉ ገልጸውታል። ስብሰባው በአፍሪካ አገሮች መካከል ያለውን የጤና ደህንነት እና ሉዓላዊነት ለማሳደግ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያንፀባርቅ መሆኑን ተናግረዋል። 

በኢትዮጵያ በስርዓተ-ምግብ ማሻሻያ እርምጃዎች በተሰራዉ ስራ ተምሳሌት የሚሆን ዉጤት ተገኝቷል - የሌሴቶ ንጉስ ግርማዊ ሌቲ ሳልሳዊ

nutrition

የሌሴቶ ንጉስ ግርማዊ ሌቲ ሳልሳዊ ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጋር በአዲስ አበባ በሚገኘው ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የህፃናት እንክብካቤ እና የስርዓተ-ምግብ ክፍልን ጎብኝተዋል፣ በጉብኝታቸው ኢትዮጵያ የእናቶችን እና የህፃናትን ጤና ለማሻሻል ያላትን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት ግርማዊ ንጉስ ሌቲ “ውጤታማ የስርዓተ-ምግብ እርምጃ ህይወትን ያድናሉ” በማለት አፅንኦት ሰጥተው፤ በኢትዮጵያ  በስርዓተ-ምግብ ማሻሻያ እርምጃዎች በተሰራዉ ስራ ተምሳሌት የሚሆን ዉጤት ተገኝቷል ብለዋል። ስርዓተ-ምግብ በሽታን በመከላከል እና የህፃናትን ሞት በመቀነስ ረገድ ያለውን ወሳኝ ሚናም ገልጸዋል። 

ንጉሱ እንዳሉት ኢትዮጵያ እናቶችን እና ህፃናትን ለመጠበቅ የምታደርገውን ጠንካራ ጥረት በገዛ ዓይናቸው ለማየት መቻላቸውን ተናግረው፤ አገሪቱ ስርዓተ-ምግብን ከጤና አጠባበቅ አደረጃጀቷ ጋር በማዋሃድ ዘላቂ የጤና ውጤቶችን ለማሳካት የሚያስመሰግን እና ስትራቴጂካዊ አቀራረብ መከተሏን ገልጸዋል።