Articles

ከክረምት ወቅት ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በቅንጅትና በትብብር መስራት ያስፈልጋል።

news

በሃገራችን የክረምት ወቅት መግባት ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ወረርሽኞች ስርጭት ሊጨምር ስለሚችል የክትትል እና የመከላከል ስራዎችን አጠናክሮ መስቀጠል እንደሚገባ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ወቅታዊ የወረርሽኞች ስርጭት መካለከልን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በተሰጠዉ ጋዜጣዊ  መግለጫ አሳስበዋል፡፡ 


በተለይም የአየር ንብረት ለዉጥ እንዲሁም ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የወባ በሽታ ስርጭት ተጋላጭነትን እንደጨመረ  ያስረዱት ዶ/ር መቅደስ፤ በለፉት 2 አመታት የወባ ወረርሽኝ በአፍሪካ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ 69 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ለወባ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ይኖራሉ ያሉት ሚኒስትሯ፤ በተለይም በክረምት ወራት የወባ ስርጭት ሊጨምር ስለሚችል  የበሽታው መከላከል እና ቁጥጥር ስራዎች ላይ ማህበረሰቡና ሁሉም ባለድርሻ አካላት  በንቃት እንዲሳተፉ ጠይቀዋል፡፡  

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን እና የአገልግሎት አሰጣጥን ጎበኙ 

jima University

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በጅማ ከተማ የሚገኘው የጅማ ዩኒቪርሲቲ ሆስፒታልን የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን፣ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የአስተዳደር ህንጻ ጎብኝተዋል፡፡ ህንጻው ከፍተኛ አቅም ያለው የዳታ ሴንተርን አካቶ የተገነባና በቀጣዩ አመት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል፡፡ 

የሆስፒታሉ የካንሰር ማእከል፣ የምርምር ላብራቶሪ፣ የጽኑ ህሙማን፣ እና ሌሎች የህክምና አገልግሎት መስጫ ክፍሎች የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችንም ዶ/ር መቅደስ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡ 

በሆስፒታሉ እየተሰጠ የሚገኘው የኬሞ እና የጨረር የካንሰር ህክምና፣ የቃጠሎ ፕላስቲክ እና ሪኮንስትራክቲቭ ሰርጀሪ፣ የአካል ጉዳት እና የድንገተኛ አደጋ ህክምና፣ እንዲሁም የማህጸን እና ጽንስ እና የህጻናት ህክምና  ክፍሎች እየሰጡ የሚገኘውን አገልግሎት መጎብኘት ተችሏል፡፡ 

የ2016 ዓ ም የጤናው ዘርፍ የክረምት በጎ አድራጎት ትግበራ ''በጎነት ለጤናችን"  በሚል መሪ ቃል ከፍለው መታከም ለማይችሉ ከ2 ሚሊዮን በላይ  ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነጻ የጤና ምርመራና ህክምና አገልግሎት ለመሰጠት በማቀድ የጤና ሚኒስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና የሚኒስትር ዴኤታዎች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል

Dr Mekdes Daba

በጤና ሚኒስቴር አስተባባሪነት የ2016 ዓ.ም የነጻ ጤና ምርመራ እና ህክምና አገልግሎት በአገር አቀፍ ደረጃ ማስጀመርያ መርሀ ግብር በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚኒሊየም የህክምና ኮሌጅ  እና በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የተጀመረ ሲሆን ሌሎች ባለድርሻ አካላትንም በማስተባበር ሙሉውን ክረምት ሲከናወን የሚቆይ ይሆናል። 

የጤና ሚኒስትር ዶክተር  መቅደስስ ዳባ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቱን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት የዘንድሮው ነጻ የጤና ምርመራና ህክምና አገልግሎት  ከፍለው መታከም የማይችሉ ዜጎችን ለማገዝ እንደሚረዳና ንቅናቄውም ''በጎነት ለጤናችን"  በሚል መሪ ሀሳብ በአገር አቀፍ ደረጃ በስፋት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።