የእናቶችና የህፃናት ጤናን ለማሻሻል የሚያግዙ 10 ተንቀሳቃሽ የህክምና ክሊኒኮችን ለመለገስ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡
የጃፓን መንግስት በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎትን ፍትሃዊና ተደራሽን ለማጠናከር የሚያግዙ የተሟላ የህክምና ቁሳቁስ ያላቸው 10 ተንቀሳቃሽ የህክምና ክሊኒኮችን ለመለገስ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ስምምነት ተፈራርሟል
በጃፓን መንግስት በኩል ስምምነቱን የፈረሙት በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታኮኮ ባስተላለፉት መልዕክት በሀገራቸው የተደረገው የ500 ሚሊዮን የጃፓን የን/3.5 ሚሊዮን ዶላር/ ድጋፍ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ክልሎች ድጋፍ የሚሹ ተብለው በተለዩት በአፋር፣ በሶማሌ፣ በቤንሻንጉል፣ በጋምቤላና በደቡብ ምዕራብ ክልሎች ያለውን የእናቶችና ህፃናት ጤና በማሻሻል የሚሞቱ እናቶችና ህፃናትን ቁጥር እንደሚቀንስ ያላቸውን ተስፋ ጠቁመው ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮቹ አልትራሳውንድና ኤሌክትሮ ካርዲዮግራፍን ጨምሮ መሰረታዊ የህክምና ቁሳቁሶችን ያሟሉ እንደሚሆኑ ገልፀዋል፡፡