Articles

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ዶ/ር አቭርሃም ንጉሴ የተመራ ልኡካን ቡድን ከጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያየ 

Israel

ኢትዮጵያ እና እስራኤል ጠንካራ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ያስታወሱት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ዶ/ር አቭርሃም ንጉሴ፤ የሁለቱ ሃገራት ወዳጅነት ከምንግዜውም በላይ ጠንካራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 
የጤና ዘርፍ ሁለቱ ሃገራት በትብብር ከሚሰሩባቸው ዘርፎች ዋነኛው መሆኑን አምባሳደሩ ያስረዱ ሲሆን፤ በተለይም በልብ ህክምና፣ የጨቅላ እጻናት ጽኑ ህሙማን እና የእናቶች ጤና እንዲሁም የአካል ድጋፍ እና መልሶ ማገገም ዘርፎች ድጋፍ የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 


እስካሁን በኢትዮጵያ ከ1000 ለሚበልጡ ይልብ ህሙማን ህክምና መስጠት የቻለው ሴቭ ቻይልድስ ሃርት ልኡካን ቡድን በጥቁር አንበሳ የልብ ማእከል የልብ ህሙማን ልየታ፣ የባለሙያዎች ስልጠና፣ እና የልብ ቀዶ ህክምና ማድረጉ በውይይቱ ተገልጿል፡፡ በተመሳሳይ የጽኑ ህሙማን ህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት እና የባለሙያዎች ስልጠና መሰጡትንም ልኡካኑ አስታውቀዋል፡፡

ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ለኢትዮጵያ የጤና አጠባበቅ እያደረገ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው - የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ

Gates Foundation

የጌትስ ፋውንዴሽን መስራችና ባለቤት ቢል ጌትስ ጋር ዉይይት ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ  በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋንን ተደረሽ ለማድረግ፣ ጤናን እና ስነ ምግብን፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥ፣ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን እና የኤስዲጂ ኢላማዎች ከግብ እንዲደርሱ ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር ጠንካራ አጋርነት መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡


የጌትስ ፋውንዴሽን መስራችና ባለቤት ቢል ጌትስ ጋር በተደረገው ውይይት ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን ሚኒስትሯ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡


እ.ኤ.አ. ከ 2018 በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ኢትዮጵያን የጎበኙት ቢል ጌትስ ከጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እና ሌሎች  የስራ ኃላፊዎች ጋርም ዉይይት አድርገዋል።

በአፍሪካ የሚከሰቱ ወረርሽኞችንና ድንገተኛ የጤና አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር “ለአፍሪካ ችግር የአፍሪካ መፍትሄ” በሚል መርህ አገራት በጋራ መስራት ይጠበቅብናል።  የኢፌድሪ ጤና ሚኒስትር፣ ዶ/ር መቅደስ ዳባ

Dr Mekdes Daba

በብራዛቪል ኮንጎ እየተካሄደ ያለዉ 74ኛው የአፍሪካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ቀጥሏል። 


በመድረኩ በአፍሪካ በተለያዩ ግዜያት ወረርሽኞችና ሌሎች ድንገተኛ የጤና አደጋዎች እየተከሰቱ የማህበረሰቡ ጤና ስጋት መሆናቸዉ አሳሳቢ መሆኑ ተገልጿል። 


ኢቦላ፣ ኮቪድ 19 እና ሌሎች ወረርሽኞች በአፍርካ ቀጠና ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን በማስታወስ አሁን ላይ ኤም ፖክስ (Mpox) የደቀነዉ የጤና አደጋ በተለይ ለአፍሪካ አሳሳቢ መሆኑ ተንስተዋል። 


በመደረኩ ላይ በመገኘት ሀሳባቸዉን ያቀረቡት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ በኤም ፖክስ (Mpox) የተጠረጠረም ሆነ የተያዘ ሰዉ አለመኖሩን ጠቅሰዉ በሽታዉ እንዳይከሰት፣ ከተከሰተም ለመቆጣጠር የሚያስችል ሰፊ የቅደመ መከላከልና ቁጥጥር ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።